የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የተለያዩ የክልል ርዕሰ መስተዳድሮች የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን፥ የህዳሴ ግድባችን ህዝባችንና መንግስታችን ከጫፍ እስከ ጫፍ በተባባረ ክንድ እየገነባነው የሚገኝ አገራችንንም ሆነ መላው አፍሪካንም የሚያኮራ ታላቅ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
በተመሳሳይ የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ በእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸው፥ የህዳሴ ግድቡ ሁለተኛ ዙር ውሃ ሙሌት መጠናቀቅ እኛ ኢትዮጵያውያን ለአላማችን በፅናት ከቆምን አንድነታችንን ካጠናከርን እና ከተባበርን ስኬታማ መሆን እንደምንችል ማሳያ ነው ብለዋል።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በደስታ መልዕክታቸው እንደገለጹት፥ ሀገራዊ አንድነትን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ማጠናከር ይገባል ያሉ ሲሆን፥ በተለይም የኢትዮጵያን እድገትና አንድነት የማይሹ የውስጥና የውጭ ሀይሎች እያደረሱ ያለውን ጫና በጋራ መመከት እንደሚገባ አስረድተዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በደስታ መልዕክታቸው፥ የክልሉ መንግስት የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ በስኬት እንዲከናወን ከገንዘብ እስከ ህይወት መስዋዕትነት የከፈላችሁ የክልላችን እና መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች ለዛሬዋ የድል ቀን በመብቃታችን እንኳን ደስ አለን ፤ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!