Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያን አንድነት የሚፈታተነውን ጁንታ ለማንበርከክ ከሰራዊታችን ጎን እንቆማለን-የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን ሠላምና አንድነት የሚፈታተነውን የሽብር ቡድን ህወሓት ለማንበርከክ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንቆማለን አሉ የኮንሶ ዞን ነዋሪዎች፡፡
ነዋሪዎቹ የኢትዮጵያውያንን ሠላምና አንድነት የሚፈታተነውን ጁንታ(ህወሓት) ለመጨረሻ ጊዜ ለማንበርከክ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ጎን መቆማቸውን በሰላማዊ ሰልፍ አረጋግጠዋል።
በሰላማዊ ሰልፉ ፈተናዎችን እየመከትን የተስፋ ብርሃናችንን ለማድመቅ እንሠራለን፣ የአሸባሪውን የህዋሃት ትንኮሳ እናከሽፋለን፣ ኢትዮጵያ ከፈተናዎቿ በላይ ሃያል ሃገር ናት፣ የአድሎ እጆች ከኢትዮጵያ ላይ ይነሱ እና የጦር መሣሪያ ከትግራይ ህፃናት ትከሻ ላይ ይነሳ የሚሉ መፈክሮች ከፍ ብለው ተደምጠዋል፡፡
የኮንሶ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዳዊት ገበየሁ ህዝቡ ለመከላከያ ሰራዊት ላሳየው ድጋፍና አጋርነት ምስጋማ ማቅረባቸውን ከኮንሶ ዞን ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሀገር ማለት እኛ ነን፤ እኛ ደግሞ የኢትዮጵያ ህዝቦች ነን ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ÷ ስለዚህ እኛን ሊለያይ፤ ሊበትን የሚችል ኃይል የለም፤አይኖርምም ሲሉ አረጋግጠዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.