Fana: At a Speed of Life!

የሕወሓት አሸባሪ ቡድን ህፃናትን ጦርነት ላይ በማሰለፍ እየፈፀመ ያለው ከባድ ወንጀል ጭካኔው ያሳየ ነው – የጨፌ አባላት

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሕወሓት አሸባሪ ቡድን ህፃናትን ወደ ጦርነት በማሰለፍ እየፈፀመ ያለው ከባድ ወንጀል ጭካኔውን ያሳየ መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት (ጨፌ) አባላት ገለጹ።

የህወሃት የሽብር ቡድን ህፃናትና ታዳጊዎችን አስገድዶ ወደ ጦርነት በማስገባት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተጠያቂ የሚያደርገውን ከባድ ወንጀል እየፈፀመ እንደሚገኝ አባላቱ አስታውሰዋል።

አባላቱ እንደተናገሩት፥ የሕወሓት አሸባሪ ቡድን የሚፈጽመው እኩይ ተግባር የኢትዮጵያን ባህልና እሴት የሚንድና ክብሯንም የሚነካ ሆኗል።

ቡድኑ በተለይም ታዳጊ ህፃናትን ለውጊያ በማሰለፉ እየፈፀመ ያለው ከባድ ወንጀል የቡድኑን ጭካኔ ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም ኢትዮጵያዊያን በአንድነት ሆነው አሸባሪውን ሃይል ሊዋጉት እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የጨፌ አባል ወይዘሮ ጠጄ ደረጄ ልጆች መማር ሲገባቸው ለጦርነት መሰለፍ እንደማይገባቸው አመልክተዋል።

የአሸባሪ ቡድኑ ህጻናትን ለጦርነት ማሰማራት ልጆች ላይ የስነ ልቦና ጫና እንደሚያስከትል የገለጹ ሲሆን፥ ድርጊቱ ሊወገዝ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ሼህ ጂያድ አባቦሪ በበኩላቸው፥ ልጆችን ለጦርነት ማሰለፍ በባህልም ተቀባይነት የሌለው ነውር መሆኑን ጠቅሰው፥ ጥፋቱ እንዲቆም መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ሌላው የጨፌው አባል አቶ ወንድሙ ቦንሳ ድርጊቱ አሸባሪው ቡድን የህብረተሰብ ጠንቅ መሆኑን ያሳየበት ድርጊት መሆኑን አመልክተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.