Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ በተወለዱ በ87 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

የከንቲባ ዘውዴ ተክሉ የቀብር ስነ ስርዓት በነገው ዕለት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ከቀኑ 6፡30 የሚፈጸም ሲሆን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቅጥር ግቢ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የፌደራል እና የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ፣ወዳጅ ዘመድ እና ቤተሰቦቻቸው በሚገኙበት ሽኝታቸው የሚከናወን ይሆናል፡፡

ከንቲባ ዘውዴ ተክሉ በ1973 ዓ.ም በተደረገው 3ኛ ዙር የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ማህበራት ምርጫ ከንቲባ በመሆን ተመርጠው ከ1973 እስከ 1981 ዓ.ም ድረስ በከንቲባነት ማገልገላቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.