Fana: At a Speed of Life!

ደራሲ ጋዲሳ ብሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ ልብ ወለድ መጽሃፍ ደራሲ ጋዲሳ ብሩ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ፡፡
 
ደራሲ ጋዲሳ “ኩሳ ገዶ” በተሰኘ የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ የረጅም ልብ ወለድ ደራሲነቱ ይታወቃል፡፡
 
ደራሲ ጋዲሳ ከአባቱ ከአቶ ብሩ ዋቃ እና ከእናቱ ወይዘሮ በጂጌ ጎንፋ በ1950 ዓ.ም በአረሲ ዞን ቦቆጂ ከተማ ነበር የተወለደው፡፡
 
በ1965 ዓ.ም በአስመራ መምህራን ኮሌጅ የዲፕሎማ ትምህርቱን የተከታተለው ደራሲ ጋዲሳ ÷ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የመጀመሪያ ዲግሪውን በስነ-ጽሁፍ እና 2ተኛ ዲግሪውን በእንግሊዘኛ ቋንቋ ስነ-ጽሁፍ አግኝቷል፡፡
 
ደራሲ ጋዲሳ በዲፕሎማ ከተመረቀ ጀምሮ አፋን ኦሮሞ በስነ ጽሑፍ እንዲበለጽግ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን÷በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ለ6 ዓመታት በመምህርነት አገልግሏል፡፡
 
የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ ውስጥ ያገለግል የነበረው ጋዲሳ ብሩ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ማበልጸጊያ ኮሚቴ ውስጥም በግንባር ቀደምትነት ተሳትፏል፡፡
 
የኦሮሞ ደራሲያን ማህበር ከመሰረቱ ሰዎች አንዱ የሆነው ጋዲሳ ብሩ ÷በተወለደ በ63 ዓመቱ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡
ኩሳ ገዶ፣ ነሙማ፣ ቡሬን ቢፈ ቶኮ ሚቲ፣ ፌዲ ገም ቶኬ እና ዳምሰ አባ የተሰኙ መጽሃፍትን ለአንባቢያን አበርክቷል፡፡
 
የደራሲ ጋዲሳ ብሩ የቀበር ስነ-ስርዓት በነገው ዕለት ቤተሰቦቹ፣ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት በአዲስ አበባ ዮሴፍ ቤተክርስቲያን የሚፈጸም ይሆናል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.