Fana: At a Speed of Life!

የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በደሴ እና ወልድያ ከተሞች እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)1 ሺህ 442ኛው የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል በደሴ እና ወልድያ ከተሞች እየተከበረ ይገኛል፡፡

የደሴ ከተማ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ከማለዳ ጀምሮ በተክቢራና በሌሎችም ሃይማኖታዊ ክንውኖች በዓሉን እያከበሩ ሲሆን፥ በፉርቃን መስጅድ የኢድ ሶላት አድርሰዋል፡፡

ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር የተቸገሩትን በመርዳትና የተፈናቀሉ ወገኖቹን በመጠየቅ ሊሆን እንደሚገባ የሃይማኖቱ ተከታዮች መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

የህዳሴ ግድቡ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት በመከናወኑም ደስታ እንደተሰማቸው የበዓሉ ተሳታፊዎች የገለጹ ሲሆን፥ በቀጣይም ለሀገር ሰላም በጋራ ልንቆም ይገባል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የአረፋ በዓል በወልድያ ከተማ እየተከበረ ሲሆን፥ የዳዕዋና የበዓሉን አስተምህሮ ለምዕመኑ ያብራሩት ኡስታዝ አብደላ መሐመድ ለሚስኪኖች እንዘን የድርሻቸውንም እንስጥ ብለዋል፡፡

ኡስታዝ መሐመድ አሕመዲን እንዳሉት፥ በሰላም ጉዳይ መደራደር የለብንም፤ ሰላም ከሌለ ኢድ የለም፤ ለሰላማችን እንፀልይ፣ ለሰላም አንትጋ ብለዋል፡፡

እዚህ ስንሰግድ ከጀርባችን የሚጠብቁን ልዩ ኃይሎች ተክቢራና ዱዓ ያስፈልጋቸዋል፥ ለደኅንነታችን ስለሚሞቱም ደጀን ልንሆናቸው ይገባል ነው ያሉት፡፡

በዓሉ ሚስኪኖችን በመርዳት፣ ተፈናቃዮችን በመዘየር በደም ልገሳ እየተከበረ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.