Fana: At a Speed of Life!

የአረፋ በዓል በባህርዳር ከተማ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 1ሺህ 442ኛው የኢድ አል አድሃ በዓል በባሕር ዳር ከተማ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሁነቶች እየተከበረ ነው፡፡

በበዓሉ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼህ ሰይድ ሙሐመድን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል፡፡

ሼህ ሰይድ ሙሐመድ በመልዕክቸው፥ በዓሉን ስናከብር የተቸገሩትን በመርዳት፣ የተራቡትን በማብላት እና በማጠጣት ኀላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

ማንኛውም አቅም ያለው የእስልምና እምነት ተከታይ በሕይዎት ዘመኑ አንድ ጊዜ ሐጂ በሚፈጸምበት ቦታ በመሄድ የሐጂ ስርዓት መፈጸም እንዳለበት ከአምላክ የተሰጠ ትእዛዝ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ሼህ ሰይድ የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል እስማኤል ለአባቱ ለኢብራሂም እና ለአምላኩ ለአላህ ታዛዥነቱን ያሳየበት በዓል መሆኑን መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

በኢድ አል አድሃ በዓል የሃይማኖቱ ተከታዮች በየዓመቱ ዘር ቀለም ቋንቋ ሳይገድባቸው ከአራቱም የዓለም ጫፍ ተገናኝተው የሚያከብሩት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ሼህ ሰይድ ይህንን ታሳቢ በማድረግ በሀገራችን በተፈጠሩ ችግሮች ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ ሰዎች ድጋፍ ማድረግ ተገቢ ነው ብለዋል፡፡

“የዚህን ዓመት በዓል ስናከብር በርካታ ሀገራዊ ድሎችን ያስመዘገብንበት ዓመት በመሆኑ ደስታችን እጥፍ ነው፥ ይህ ደስታችን እንዲቀጥል ሁላችንም ኀላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ነው ያሉት፡፡

ፕሬዚዳንቱ ሀገር ወደ ተሻለ ጉዞ እንድታቀና ሁሉም በገንዘብ በጉልበት እና በሀሳብ በማገዝ ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን፥ በተለያየ ችግር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በጸሎት ማሰብ እንደሚገባም መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.