Fana: At a Speed of Life!

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ለአርቲስት ሐዋ የበዓል ስጦታ አበረከተ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ካሳው የሶማሌኛ ሙዚቃ ተጫዋጭ በነበረችው አርቲስት ሐዋ ተለል መኖሪያ ቤት ተገኝተው የበዓል ስጦታ አበርክተዋል፡፡

አርቲስት ሐዋ ተለል በአሁኑ ወቅት በዝቅተኛ የኖሩ ደረጃ ላይ የምትገኝ በመሆኑ ከድጋፉ ባለፈም የምትኖርበትን ቤት ለማደስ ሥራው ተጀምሯል፡፡

የባሕልና ቱሪዝም ሚኒስቴር የክረምት በጎ ፈቃድ አግልግሎቱ የሐዋን ቤት በማደስ የጀመረ ሲሆን ÷በቀጣይም የ10 አቅመ ደካማ አርቲስቶችን ቤት እንደሚያድስ አስታውቋል፡፡

አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ በሚገኙበት በአራዳ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ጣሊያን ሰፈር ነዋሪ የሆነችው ሀዋ የእድሳቱ ማስጀመሪያ በአረፋ በአል እለት በመከናወኑ መደሰቷን ገልፃለች ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.