Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በኢትዮጵያ አንድነት ላይ የቃጣውን ጥቃት እንደዚህ ቀደሙ በጋራ በመቆም ማክሸፍ ይገባል-አቶ ተመሰገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 13 ፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ መረጃ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተመሰገን ጥሩነህና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጎንደር ከተማ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫው አቶ ተመሰገን አሸባሪው ህወሓት ጦርነቱ ከአማራ ጋር ብቻ በማስመሰል ኢትዮጵያን ለማፈራረስ ጥረት እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ጦርነቱ ከአማራ ህዝብ ጋር እያስመሰለው የሚገኘው ራሱ ጁንታው ነው ያሉት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ÷ይህ የከፋፍለህ ግዛ ሀሳብ አሸባሪው ቡድን የኖረበትና ኢትዮጵያን ለመከፋፋል የሚጠቀምበት ነውም ብለዋል።

አሸባሪው ቡድን በአንድ በኩል ችግሬ ከአማራ ሊሂቃን ጋር ነው ቢልም በአፋር ክልል ላይ የፈፀመው ጥቃት የአሸባሪ ቡድንን ኢትዮጵያን የማጥቃት  ዓላማውን  በግልፅ የሚያመላክት ነውም ብለዋል።

አሸባሪ ቡድኑ ከአማራ በመውረድ  ሂሳብ የማወራርደው ከጎንደር ጋር ነው የሚል ሀሳብን የሚያረምደው ኢትዮጵያውያን ከፋፍሎ ለማጥቃት መሆኑን በመረዳት ከዚህ ቀደም እንደታየው አንድነትን በመጠበቅ ዓላማውን ማክሸፍ ይገባልም ነው ያሉት።

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ÷ ኢትዮጵያውያን ከጥንት ጀምሮ አንድነታችን በማስጠበቅ ብዙ ፈተናዎችን አልፈናል ፣ አባቶቻችን ኢትዮጵያ ፈተና በወደቀችበት ወቅት በአንድነት በመቆም የከፈሉትን መስዋዕትነት በመክፈል በሀገር ላይ የተቃጣውን አደጋ መመከት አለብን ሲሉ ተናግረዋል ።

አሸባሪው ህወሓት ሀይማኖት ከሀይማኖት ብሄርን ከብሄር በመከፋፈል ዓላማውን ለማሳካት መጣሩ የማይቀር ቢሆንም ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደአባቶቻቸን በጋራ በመቆም እና መስዋዕትነት በመክፈል ሀገራችንን እንስቀጥላለን ብለዋል።

ጠላት የሚነዛቸውን አሉባልታዎች ወደኋላ በመተው የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ በመሻገር ኢትዮጵያን ማስቀጠል ይገባል ብለዋል።

በክብረወሰን ኑሩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.