Fana: At a Speed of Life!

በሀገራችን ላይ የተቃጣው ጥቃት ለመመከት ከመከላከያ ሰራዊት ጎን እንቆማለን-አቶ ደስታ ሌዳሞ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከመከላከያችን ጎን በመቆም የኢትዮጵያን ዳር ድንበር እናስከብራለን አሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ።
ርዕሰ መስተዳድሩ ይህን ያሉት የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች የህዳሴ ግድብ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁን ተከትሎ ደስታቸውን ለመግለጽ ባካሄዱት ሰልፍ ላይ በተገኙበት ወቅት ነው።
ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጥ የለውጡ ትሩፋት መሆኑንም አውስተዋል።
ግድቡን ለማሰናከል ጠላቶች ብዙ ቢደክሙም የሙሌት ሥራውን ከማከናወን ሊያስቆሙን አልቻሉም፤ ወደፊትም አያስቆሙንም ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ።
ለግድቡ ከኢትዮጵያውያን የተዋጣውን ገንዘብ ህወሓት በመዝረፍ ሀገራችንን የማዳከም ሥራ ሲሰራ ቆይቶቷል ያሉት አቶ ደስታ ሌዳሞ÷ ይህንና ሌሎችም ሀገር አጥፊ ተልዕኮዎቹን አጥብቀን እንቃወማለን ብለዋል።
ከልማታችን የሚያስቆመን አንዳችም ሀይል እይኖርም፤ ግድቡ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ሙሉ ድጋፍ እናደርጋለን ማለታቸውን ደሬቴድ ዘግቧል፡፡
ጁንታውን እንቃወማለን፣ ከመከላከያችን ጎን በመቆም የሀገራችንን ዳር ድንበር እናስከብራለን ሲሉም ርዕሰ መስተዳድሩ ለሰልፉ ለታዳሚዎች ገልጸዋል።
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ በበኩላቸው ÷ የህዳሴ ግድብ 2ኛው ዙር ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ ለከተማው ነዋሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ይህ ስኬት የዜጎች አንድነት እና መተባበር ውጤት መሆኑን በመግለጽ በቀጣይም መሰል ስራዎችን በማጠናከር ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ መጠበቅ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.