ዓለምአቀፋዊ ዜና

አሜሪካ በሶማሊያ በሸመቁ የአልሸባብ አሸባሪዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈፀመች

By Alemayehu Geremew

July 21, 2021

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ በሶማሊያ በሸመቁ የአልሸባብ አሸባሪዎች ላይ የአየር ጥቃት ፈፀመች፡፡

የአሜሪካ የመከላከያ ዕዝ ማዕከል ፔንታጎን እንዳስታወቀው÷ የአሜሪካ ኃይሎች የአየር ላይ ጥቃቱን የፈፀሙት ከአልቃይዳ ጋር ግንኙነት አለው በተባለው የአልሸባብ ቡድን ላይ ነው፡፡

የፔንታጎን ቃል አቀባይ ሲንቲያ ኪንግ እንዳሉት፥ እርምጃው የተወሰደው ጋልካዮ በምትባል አካባቢ ባሉ የአልሸባብ አሸባሪዎች ላይ ነው፡፡

ጥቃቱ የተፈጸመው የሀገሪቷ መንግስት ከአሜሪካ እና ከአፍሪካ እዝ ኃይል ጋር በመተባበር እንደሆነም ታውቋል፡፡ ቅዳሜ በደቡብ ሶማሊያ ግዛት በመካከለኛው ጁባ አካባቢ የምትገኝ ጂሊብ በምትባለው ስፍራ በተወሰደው እርምጃ የ52 የአልሸባብ ተዋጊዎች ሕይወት እንዳለፈ ይታወሳል፡፡ ምንጭ ÷ሲጂቲኤን

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!