Fana: At a Speed of Life!

የአብዬ 25ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ ሰላም በማስከበር የሚያኮራ ውጤት ማስመዝገቡን ገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አብዬ የሚገኘው የ25ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ባለፉት ስድስት ወራት ሰላም በማስከበር በፈፀመው ግዳጅ ሀገርን የሚያኮራ ውጤት ማስመዝገቡን አስታወቀ፡፡
የሻለቃው ዋና አዛዥ ኮሎኔል ሌንጮ ኤደኦ እንደገለፁት፥ ሻለቃው ሲቪሎችን ከጥቃት በመከላከል፣ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅና ሰብዓዊ ድጋፍ እንዲደርስ በማድረግ በኩል ውጤታማ ሥራ ሰርቷል፡፡
ሰላም አስከባሪው ማንኛውንም አይነት ፀረ-ሰላም እንቅስቃሴና ድርጊት በሰላማዊ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ብቻ ለመፍታት ከአካባቢው የጎሳ መሪዎች ጋር በጋራ በርካታ ስራዎችን እንደሰራ መግለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በአካባቢው በህገ ወጥ መንገድ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ተከታትሎ ትጥቅ በማስፈታትና ለፖሊስ በማስረከብ እንዲሁም ራሱንና የአካባቢውን ማህበረሰብ ብሎም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኞችን ከጥቃት በመከላከል ረገድ ውጤታማ ስራ መሰራቱንም ነው የተናገሩት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.