Fana: At a Speed of Life!

በዓለም ባንክ የውሃ ግሎባል ዳይሬክተር የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በዓለም ባንክ የውሃ ግሎባል ዳይሬክተር ጄኒፈር ሳራ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባስልጣን የቃሊቲ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያን ጎበኙ።

የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ዘሪሁን አባተ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እየሰራ ያለውን ስራ እና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎችን በተመለከተ አጭር ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ከዚህ ባለፈም ባለስልጣኑ እየሰጠ ስላለው የአቅም ግንባታ ስልጠና እና እያመጣ ያለውን ለውጥ በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዳሬክተሯ ጄኒፈር ሳራ በበኩላቸው አሁን እየተሰራ ባለው ስራ መደሰታቸውን ጠቅሰው፥ በቀጣይ ባለስልጣኑ በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም ገልፀዋል።

በተለይም የፍሳሽ ቆሻሻ አጣርቶ ማስወገድ እና መልሶ መጠቀም፣ በአቅም ግንባታ፣ በተፋሰስ ልማት፣ በሂሳብ አስተዳደር እና መሰል ስራዎች ላይ ድጋፍ እንደሚደርጉ መናገራቸውን ከባለስልጣኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.