Fana: At a Speed of Life!

የደራሲ ጋዲሳ ብሩ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ  

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ ልብ ወለድ መጽሃፍ ደራሲ ጋዲሳ ብሩ የቀብር ስነ ስርዓት ተፈጸመ፡፡

የቀበር ስነ-ስርዓቱ  ቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ በተገኙበት በአዲስ አበባ ቅዱስ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያን በዛሬው ዕለት ተፈጽሟል፡፡

ደራሲ ጋዲሳ ከአባቱ ከአቶ ብሩ ዋቃ እና ከእናቱ ወይዘሮ በጂጌ ጎንፋ በ1950 ዓ.ም በአርሲ ዞን ቦቆጂ ከተማ ነበር የተወለደው፡፡

ደራሲ ጋዲሳ “ኩሳ ገዶ” በተሰኘ የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ የረጅም ልብ ወለድ ደራሲነቱ ይታወቃል፡፡

በ1965 ዓ.ም በአስመራ መምህራን ኮሌጅ የዲፕሎማ ትምህርቱን የተከታተለው ደራሲ ጋዲሳ ÷ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲም የመጀመሪያ ዲግሪውን በስነ-ጽሁፍ እና 2ተኛ ዲግሪውን በእንግሊዘኛ ቋንቋ ስነ-ጽሁፍ አግኝቷል፡፡

ደራሲ ጋዲሳ በዲፕሎማ ከተመረቀ ጀምሮ አፋን ኦሮሞ በስነ ጽሑፍ እንዲበለጽግ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርግ የቆየ ሲሆን÷በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲም ለ6 ዓመታት በመምህርነት አገልግሏል፡፡

የኢትዮጵያ ቋንቋዎች አካዳሚ ውስጥ ያገለግል የነበረው ጋዲሳ ብሩ የአፋን ኦሮሞ ቋንቋ ማበልጸጊያ ኮሚቴ ውስጥም በግንባር ቀደምትነት ተሳትፏል፡፡

የኦሮሞ ደራሲያን ማህበር ከመሰረቱ ሰዎች አንዱ የሆነው ጋዲሳ ብሩ ÷ በተወለደ በ63 ዓመቱ ነው ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው፡፡

ደራሲ ጋዲሳ ኩሳ ገዶ፣ ነሙማ፣ ቡሬን ቢፈ ቶኮ ሚቲ፣ ፌዲ ገም ቶኬ እና ዳምሰ አባ የተሰኙ መጽሃፍትን ለአንባቢያን አበርክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.