Fana: At a Speed of Life!

ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለልዩ ሃይልና ሚሊሻ ድጋፍ ማድረጋችን እንቀጥላለን – የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 14፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከአሸባሪው ህወሓት የተቃጣውን ጥቃት በጋራ ለማክሸፍ መስዋዕት እየከፈለ ላለው መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ድጋፍ ማድረጋችን እንቀጥላለን አሉ የሰሜን ሸዋ ዞን ነዋሪዎች።
ነዋሪዎቹ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ÷ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እየሰራ ያለው የሽብር ቡድን ህወሓት ፈጽሞ እንደማይሳከለት ተናግረዋል፡፡
የሽብር ቡድኑን አላማ ለማክሸፍም የህይወት መስዋዕትነት እየከለፈ ለሚገኘው መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ጻድቅ በበኩላቸው÷ ለመከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ በሶስት ቀናት ውስጥ 42 ሚሊየን ብር ድጋፍ ማሰባሰብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የህወሓትን ሃገር የማፍረስ ህልም ቅዠት ለማድረግ በጋራ ልንቆም ይገባል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ÷ ማህበረሰቡ በቀጣይ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በተለይ ወጣቱ ከጸጥታ መዋቅሩ ጋር በቅንጅት በመስራት የአካባቢውን ሰላም መጠበቅ እንደሚገባው አሳስበዋል፡፡
በሳምራዊት የስጋት
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.