ኢትዮጵያ በ3ኛው አካታች እና የተመጣጠነ ዓለም አቀፍ የትምህርት ጉባኤ ላይ እየተካፈለች ነው
አዲስ አበባ ፣ ጥር 18 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በጂቡቲ እየተካሄደ ባለውና በ3ኛው ዓለም አቀፍ አካታች እና የተመጣጠነ የትምህርት ጉባኤ ላይ እየተካፈለች ትገኛለች።
በጉባኤው ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ ሃገራት አካታች እና የተመጣጠነ ዓለም አቀፍ የትምህርት ድንጋጌ ትብብር ማዕቀፍ ቻርተርን ተፈራርመዋል።
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌህ አካታች እና የተመጣጠነ ትምህርት በ2030 ለመድረስ የተያዘውን ዘላቂ የልማት ግብ ለማሳካት ያግዛል ብለዋል።
በጉባኤው ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሂሩት ወልደማርያምን ጨምሮ የደቡብ አሜሪካ፣ የካሪቢያን፣ የእስያ እና የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የትምህርት ሚኒስትሮች እየተሳተፉ ነው።
ከዚህ ባለፈም የተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮችም የጉባኤው ተሳታፊዎች ናቸው።
በጉባኤው ሃገራት ለዘርፉ የሚመድቡትን ገንዘብ እንዲያሳድጉ መጠየቁን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።