Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ የደቡብ ክልል ልዩ ሀይል አባላት ወደግዳጅ ቀጠና ያመራሉ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ተጨማሪ የደቡብ ክልል ልዩ ሀይል አባላት ወደግዳጅ ቀጠና ያመራሉ።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን ሃገር ላይ የጋረጠውን አደጋ ለመቀልበስ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እየሰሩ ይገኛሉ።

የደቡብ ክልል ልዩ ሀይል ሀገራዊ ጥሪውን በመቀበልም ከጀግናው የመከላከያ ሰራዊት ጎን መቆሙን ትግሉን በመቀላቀል አረጋግጧል።

ከ300 የሚበልጡ የልዩ ሀይል አባላት በአሁን ወቅት ሀገራዊ ግዳጃቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ ደግሞ ተጨማሪ የክልሉ ልዩ አባላትም ወደ ግዳጅ ቀጠና ያመራሉ።

በሀዋሳ አለም አቀፍ ስታዲየም የጀግና ሽኝት ይደረግላቸዋል ተብሎ  እንደሚጠበቅ ከደቡብ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.