የሀገር ውስጥ ዜና

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ 2ኛውን በረራ ሊያደርግ ነው

By Meseret Demissu

July 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ  ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አየር ማረፊያ ወደ መቐለ 2ኛውን በረራ ሊያደርግ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት የተናጠል ተኩስ አቁም ካወጀ ወዲህ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ 2ኛውን የአውሮፕላን በረራ ሊያደርግ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በዚህ በ2ኛው የዓለም ምግብ ፕሮግራም በረራ ከ30 በላይ የሚሆኑ ግለሰቦች እና የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ሰራተኞች እንደተካተቱም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር  ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!