የሀገር ውስጥ ዜና

በሀዲያ ዞን አሸባሪው ህወሓትን የሚቃወምና መከላከያን የሚደግፍ ሰልፍ ተካሄደ

By Meseret Awoke

July 22, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀዲያ ዞን የአሸባሪውን የህወሓት ጁንታን የሚቃወምና መከላከያ ስራዊትን የሚደገፍ ሰልፍ ተካሂዷል።

በሆሳዕና ከተማ ዛሬ የተካሄደው ሰልፍ ከዞኑ ከሁሉም ወረዳዎችና ከተሞች የተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የአስተዳደር አካላት፣ መካላከያ ሰራዊትና የፖሊስ አባላት መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያን ክብር አሳልፎ የሚሰጥ ትውልድ የለም፣ የጦር መሳሪያ ከትግራይ ህፃናት ትከሻ ላይ ይውረድ፣ ከመከላከያ ሰራዊት ጎን በመሆን እንደ ሀገር የተጀመረውን ለውጥ እናስቀጥላለን የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በማሰማት ለህወሓት ያላቸውን ተቃውሞና ለመከላከያ ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!