Fana: At a Speed of Life!

በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሌሎች ለሚፈጥሩት ሀሳብ መልስ ከመስጠት ተላቀን በራሳችን አጀንዳ የምንሰጣቸው መሆን አለበት- የዘርፉ ምሁራን

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ሌሎች ለሚፈጥሩት ሀሳብ መልስ ከመስጠት ተላቀን በራሳችን አጀንዳ የምንሰጣቸው መሆን አለበት ሲሉ የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።
የታላቁ ህዳሴው ግድብ የተጋረጠበትን ዲፕሎማሲያዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫናዎችን ተቋቁሞ ዛሬ ላይ የሁለተኛው ዙር ሙሌት በስኬት ተጠናቋል።
በዚህ ሂደት ደግሞ የኢትዮጵያን እውነት በማስረዳት ረገድ በተካሄደው እልህ አስጨራሽ ትግል እና ፈተና ዜጎች በዲጂታል ሚዲያዎች ያደረጉት ተጋድሎ ከፍ ብሎ ይታያል።
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያነጋገራቸው እና በተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ስለ ግድቡ እውነት እየሞገቱ ያሉት መሀመድ አል አሩሲ፣በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና ኢሲያ ጥናት እና ምርምር ማእከል ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተፈራ እና የአለም አቀፍ ግኑኝነት ምሁሩ ሱሌይማን አራጋው አሁንም ያልተቋጨው የህዳሴ ዶሴ እና ሌሎችም የልማት ስራዎቻችን ከፊት ይጠብቁናል እና ለዚህ መዘጋጀት ይኖርብናል ብለዋል።
መንግስት እነዚህን በፍላጎታቸው ለግድቡ እየተከራከሩ ያሉትን ዜጎች ማደራጀት፣ማገዝ እና የተለያዩ ስልጠናዎችንና መረጃዎችን በቅርበት እንዲያገኙ ማድረግ ላይ በሰፊው ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
በተለያዩ አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እውነትን ይዞ ግብጾች እና ሌሎች የአረብ ሀገራት የያዙትን ከእውነት የራቁ ሀሳቦችን በመሞገት የሚታወቀው መሃመድ ከማል አሊ አል አሩሲ ÷ እስካሁን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አማራጮች ለአለም በደረሱት መረጃዎች ከዚህ ቀደም ስለ ህዳሴው ግድብ ሲወሩ የነበሩት ውሸቶች እየተጋለጡ ነው ብሏል።
የዲጂታል ዲፒሎማሲ ተሳታፊዎቹ አባይ ከ60 በመቶ በላይ ለሚሆኑት ዜጎች መብራት ሊሆን እየተገነባ ስለመሆኑ ደጋግመው አጽንኦት ሰጥተው ለአለም አቀፍ ማህበረሰቦች አስረድተዋልም ነው ያለው።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ እና እስያ ጥናት እና ምርምር ማእከል ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተፈራ÷ ግድቡ የኢኮኖሚ ትስስር የመፍጠር ትልቅ አቅም ያለው ፣ በጋራ የመልማት ትልቅ መሰረተ ድንጋይ የሚያስቀምጥ ፕሮጀክት ስለመሆኑ መብራራት መቻሉን ተናግረዋል።
በአለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ሱሌይማን አራጋው በበኩላቸው÷ የህዳሴ ግድብ አንደኛው እና ሁለተኛው የውሃ ሙሌት ስኬት ጀርባ የግብጽና የሌሎች ምዕራባዊያን ማስፈራሪያ እና ያልተጨበጡ መረጃዎችን በማጋለጥ ረገድ ከሁሉም ማዕዘናት ዜጎች የከፈሉት አስተዋጽኦ ዘመናትን የሚሻገር ነው ብለዋል።
በአፈወርቅ አለሙ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.