Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል በአፍሪካ ሕብረት ውስጥ የታዛቢነት ቦታ አገኘች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ያይር ላፒድ ይህ ቀን የእስራኤልንና የአፍሪካን ግንኙነት በደስታ የምናከብርበት ነው ብለዋል፡፡

ለዲፕሎማሲያዊ ስኬቱም የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ትብብር እና በህብረቱ አባል ሀገራት የሚገኙ የእስራኤል ኤምባሲዎች ጥረት ከፍተኛ ሚና እንደነበራቸው ገልፀዋል፡፡

ያይር አያይዘውም እስራኤል በህብረቱ የታዛቢነት ቦታ ማግኘቷ ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት ተቀዛቅዞ የቆየውን ግንኙነት የምታድስበትና በቀጣይ የተለያዩ ስራዎችን ከአህጉሩ ብሎም ከህብረቱ አባል ሀገራት ጋር የምትሰራበት ጊዜ ይሆናልም ነው ያሉት፡፡

እስራኤል ከ55ቱ የህብረቱ አባል ሀገራት ከ46ቱ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላት ሲሆን፥ ከሞሮኮ እና ሱዳን ጋር አቋርጣ የነበረውን ግንኙነትም ባለፈው አመት ዳግም አድሳለች፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.