Fana: At a Speed of Life!

ከተማ አስተዳደሩ በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎች ዕውቅና ሰጠ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮቪድ19 ወረርሽኝ ወቅት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎችና የክብካቤ ሰራተኞች ዕውቅና ሰጠ።
በመርሃግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ በወረርሽኙ ወቅት ግንባር ቀደም በመሆን ወገኖችን በመታደግ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የከተማ አስተዳደሩ ምስጋናና ዕውቅና እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ባለፈ በወረርሽኙ ምክንያት የሚያጋጥሙ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሰራ ጠቁመዋል ።
የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ዮሃንስ ጫላ በበኩላቸው ÷የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ከፍተኛ ቢሆንም ነዋሪዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ለከፋ ጉዳት እንዳይጋለጡ የጤና ባለሙያዎች እና የክብካቤ ሰራተኞች የበኩላቸውን በማድረግ እስከ ህይወት መስዋዕትነት በመክፈል አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ተናግረዋል ።
በመርሃ ግብሩ የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሕክምና ባለሙያዎች ፣ የመንግሥትና የግል ጤና ተቋማት፣የኮቪድ -19 ማገገሚያ ማዕከላት ውስጥ የሚያገለግሉ የክብካቤ ሰራተኞች የዕውቅና ሽልማት መበርከቱን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.