Fana: At a Speed of Life!

የቁልቢ ገብርኤል በዓለ ንግስ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ ተገብቷል-ፖሊስ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቁልቢ ቅዱስ ገብርኤል በዓለ ንግስ ያለምንም የፀጥታ ችግር እና የትራፊክ አደጋ እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ወደ ስራ መግባቱን የድሬደዋ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በዓለ ንግሱ ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል ለሁሉም ፈፃሚ አመራር እና አባላት እንዲሁም አጋዥ ተቋማት በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ ከማድረግ ጀምሮ ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሰራታቸው ተመላክቷል፡፡
በዓሉ ያለምንም የፀጥታ ችግርና የትራፊክ አደጋ በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ ለማስቻል በስውርና በግልፅ የሰው ሃይል በመመደብ ወደ ስራ መገባቱ ነው የተገለጸው፡፡
ከበዓሉ ጋር ተያይዞ ወደ ከተማው የሚመጡ እንግዶች ራሳቸውን ከተለያዩ የስርቆትና ሌሎች መሰል የወንጀል ድርጊቶች መጠበቅ እንዳለባቸው አሳስቧል፡፡
እንግዶች የተለዩ አጠራጣሪ ጉዳዮች ሲያጋጥማቸውም ወዲያውኑ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠ ይኖርባቸዋል ነው ያለው ድሬ ፖሊስ ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት፡፡
ለበዓሉ ሰላማዊነት ሁሌም ከፖሊስ ጋር ተባብሮ የሚሰራውና ለሰላሙ ቅድሚያ የሚሰጠው መላ የአስተዳደሩ ነዋሪ አሁንም ከፖሊስና ከሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ጎን በመሆን ይበልጥ አብሮ እንዲሰራም ጥሪ ቀርቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.