የሀገር ውስጥ ዜና

የጋሞ ዞን ነዋሪዎች ለመከላከያ ሰራዊት የድጋፍ ሰልፍ አደረጉ

By Tibebu Kebede

July 24, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋሞ ዞን ነዋሪዎች መከላከያ ሰራዊቱን በመደገፍ በአርባምንጭ ከተማ ሰልፍ እያካሄዱ ነው፡፡

በአሸባሪው የህወሓት ቡድን ሴራ ኢትዮጵያ አትፈርስም፣ የቡድኑን ህገወጥ ተግባር የዓለም መንግስታትም ሊያወግዙ ይገባል፣ የቡድኑን ትንኮሳን በተባበረ ክንድ እናከሽፋለን፣ የራሳችን ሀብት የሆነውን አባይን ተጠቅመን ልማታችንን እናፍጥናለን ፣ ለግድባችን የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንቀጥላለን የሚሉና መሰል መልዕክቶችንም በሰላሚዊ ሰልፉ አስተጋብተዋል።

ምንጭ፡- ደሬቴድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!