Fana: At a Speed of Life!

በህንድ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ 110 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ ከባድ ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ እና የመሬት መንሸራተት 110 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸው ተሰማ፡፡

በአደጋው ለህልፈት ከተዳረጉት በተጨማሪ በርካቶች መጎዳታችውም ነው የተነገረው፡፡

በከፍተኛ ወጀብና አውሎ ነፋስ የታጀበው ዝናብ ማሃራሻትራ በተሰኘችው የሃገሪቱ ምዕራባዊ ግዛት የደረሰ ነው ተብሏል፡፡

በበርካታ ከተሞች የመሰረተ ልማት ውድመት የደረሰ ሲሆን፥ የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡንም የሃገሪቱ ባለስልጣናት ገልጸዋል፡፡

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም አደጋው በደረሰባቸው አካባቢዎች የነብስ አድን ስራ እያከናወኑ ነው፡፡

ይሁን እንጅ በአካባቢዎቹ ያለው አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ የነብስ አድን ስራውን አስቸጋሪ እንዳደረገው የቢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.