Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ የሀገር መከላከያ ሠራዊትን በመደገፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍና አሸበሪዊን የህወሓት ቡድን የሚቃወም ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በድሬደዋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ነዋሪዎቹ በያዙት መፈክርና በአንደበታቸው “ኢትዮጵያ አሸንፋለች ፣ወደ ፊትም ታሸንፋለች”፣ “እኛ ድሬዎች ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን ነን” ፣ “ክብርና ሞገስ ውድ ህይወታቸውን ለሰጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት” ፣ “እኛ ኢትዮጵያውያን ሰላማችንን በማስጠበቅ ልማታችንን እናረጋግጣለን” የሚሉ መልዕክቶችን አስተላልፈዋል ።

በተጨማሪም “አሸባሪው ህውሃት ጁንታ በዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለውን የግፍ ስራ በፅኑ እንቃወማለን” ፣ “አገር በጁንታው ሴራ አትፈርስም”፣ “የህልውናችን መሠረት የሆነው የህዳሴ ግድባችንን እስከመጨረሻው በመደገፍ ከዳር እናደርሳለን”  ፣ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በድል መጠናቀቅ ደግሞ የበለጠ አነቃቅቶናል” የሚሉ እና በርካታ መፈክሮች በጋራ በማሰማት ላይ ናቸው ።

ከዋና ዋና አደባባይ ሰልፍ በመለስ ደግሞ በአሁን ሰአት በድሬዳዋ ለገሀር አደባባይ ሰልፈኞቹ እየተሰበሰቡ ናቸው።

በአደባባይ ለተሰበሰበው ነዋሪ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ ቡኽ መልዕክት ያስተላልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በተጨማሪም የድሬዳዋ ሴቶች እና ወጣቶች ፌደሬሽኖች አመራሮች መልዕክት ያስተላልፋሉ ።

ሠራዊቱን በሚደግፈውና ሽብርተኛውን የህወሓት ጁንታ የሚያወግዘው ሰልፍ ላይ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ በየደረጃው የሚገኙ ነዋሪዎች፣የድሬዳዋ አስተዳደር አመራሮች፤የአገር ሽማግሌዎች ተሳታፊዎችመሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.