Fana: At a Speed of Life!

የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንደሚሰለፉ አረጋገጡ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት አባላት በማንኛውም ግዳጅ ከመከላከያ ሠራዊቱ ጎን እንደሚሰለፉ አረጋግጠዋል።
አባላቱ ይህን ያረጋገጡት “ኢትዮጵያን ማፍረስ አይቻልም ፣ ምክንያቱም ሰው አለ!!” በሚል መሪ ቃል በቀድሞ የሠራዊት አባላት የድጋፍ እና የልማት ማኅበር አነሳሽነት በመስቀል አደባባይ በተካሄደው ዝግጅት ላይ ነው።
በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የመከላከያ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ÷ የቀድሞ የሠራዊት አባላት ለሀገራቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ በግፍ በትኗቸው ከነበረው የሕወሓት ቡድን ጋር ጭምር ሀገር ስትወረር ቀድመው በመሰለፍ በተለያዩ ወታደራዊ ሙያዎች ሀገራቸውን ማገልገላቸውን አስታውሰዋል።
አሁንም ሀገር በፈለገቻቸው ወሳኝ ወቅት በራሳቸው ተነሳሽነት ከሠራዊቱ ጎን ለመሰለፍ ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል።
የማኅበሩ ሰብሳቢ ሃምሣ አለቃ ብርሀኑ አማረ በበኩላቸው÷ የመከላከያ ሠራዊቱ ሀገርን ለመበታተን ከተነሡ ኃይሎች ጋር የሚያደርገውን ትግል በሙያቸው ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።
የቀድሞ የኢትዮጵያ ሠራዊት የድጋፍ እና የልማት ማኅበር በመላ ሀገሪቱ 287 ቅርንጫፍ እና ከአንድ ሚሊየን በላይ አባላት ያሉት መሆኑን ከመከላከያ ሠራዊት የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
+2
0
People Reached
0
Engagements
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.