Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል1 ሺህ 700 በላይ ሰንጋ እና 1 ሺህ 800 በላይ በግ እና ፍየል ለመከላከያ ሰራዊት አስረክቧል

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 18፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል እስካሁን ለመከላከያ ሰራዊት ከ 1 ሺህ 7 00 በላይ ሰንጋ እና 1 ሺህ 80 በላይ በግ እና ፍየል ድጋፍ ማድረጉን የመከላከያ ድጋፍ የክልሎች አስተባባር ኮሚቴ አስታውቋል፡፡

የኮሚቴው አስተባባሪ ዶክተር ተመስገን ቡርቃ÷ በዛሬው ዕለት የሆሩ ጉድሩ ዞን፣ የጉጂ ዞንና የቢሾፍቱ ከተማ 111 ሰንጋና 100 በግና ፍየል ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡

የዛሬውን ጨምሮም የኦሮሚያ ክልል እስካሁን ለመከለከያ ሰራዊት ከ 1 ሺህ 7 00 በላይ ሰንጋ እና 1 ሺህ 80 በላይ በግ እና ፍየል ድጋፍ ማድረጉን  ነው የገለጹት፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ማርታ ሉዊጅ በበኩላቸው÷ ክልሉ ያደረገው ድጋፉ ለሀገር ሉዓላዊነት መከበር እና ሰላም መስፈን እንዲሁም የህልውና ዘመቻውን በድል ለማጠናቀቅ የሞራል ስንቅ እንደሚሆን አውስተዋል፡፡

በተጨማሪም ድጋፉ ህብረተሰቡ ከሰራዊቱ ጎን መቆሙን እና እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተገቢ መሆኑን ያሳየበት መሆኑን በማንሳት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በሌላ በኩል የትግራይ ክልል ወጣት ለፖለቲካ ትርፍ ተብሎ ከኢትዮጵያዊያን መለየት ከማይችሉበት የቤተሰብነት ትስስር ሊነጥላቸው ለሚችል እኩይ ተግባር ተሰልፈው ለጥይት ሲሳይ ከመሆን ቆም ብለው ማሰብ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ኢትዮጵያ ደህንነቷን ጠብቃ እንድትራመድ ሁላችንም በተሰማራንበት መስክ ሁሉ በቅንጅት ልንሰራ ይገባናል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ በድጋፉ የታየውን ትብብር በልማቱም ማስቀጠል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

የመከላከያ ሰራዊት  የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ኮሎኔል ጌትነት አዳነ÷ ይህ ድጋፍ ከድጋፍነቱ ባለፈ ለመከላከያው የአለሁልህ ስነ ልቡናዊ አለኝታነቱ ትልቅ መልዕክት ያዘለ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ድጋፉ ህዝባችን አብሮን መሆኑን እና ደጀናችን መሆኑን የሚያረጋግጥ በመሆኑ በቀጣይምተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አመላክተዋል።

 

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.