Fana: At a Speed of Life!

በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን እገታ የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን የእገታ ድርጊት የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተካሄዱ ።

ሰላማዊ ሰልፎቹ በዩኒቨርሲቲው ሲማሩ የነበሩና የታገቱ ተማሪዎችን በተመለከተ መንግስት ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ፣ በአጋቾች ላይም እርምጃ በመውሰድ የሕግ የበላይነትን እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል።

የእገታ ድርጊቱን ኢ-ሰብዓዊ እና ከኢትዮጵያዊነት እሴት ያፈነገጠ ነው ሲሉ የሰልፉ ተሳታፊዎች ኮንነውታል።

ሰላማዊ ሰልፎቹ በባህር ዳር፣ ደብረማርቆስ፣ ወልዲያ፣ ቆቦ፣ ሸዋ ሮቢት፣ ዱር ቤቴ፣ ዳንግላ፣ ደብረ ብርሃን፣ ፍኖተ ሰላም እና በሌሎች ከተሞች ነው የተካሄዱት።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.