የሀገር ውስጥ ዜና

በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን እገታ የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተካሄዱ

By Tibebu Kebede

January 28, 2020

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የተፈጸመውን የእገታ ድርጊት የሚያወግዙ ሰላማዊ ሰልፎች በአማራ ክልል በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተካሄዱ ።

ሰላማዊ ሰልፎቹ በዩኒቨርሲቲው ሲማሩ የነበሩና የታገቱ ተማሪዎችን በተመለከተ መንግስት ግልጽ መረጃ እንዲሰጥ፣ በአጋቾች ላይም እርምጃ በመውሰድ የሕግ የበላይነትን እንዲያረጋግጥ ጠይቀዋል።