Fana: At a Speed of Life!

በኢሉባቦር ዞን በፍቃደኝነት መከላከያን ለመቀላቀል የወሰኑ ወጣቶች ተሸኙ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢሉባቦር ዞን በፍቃደኝነት መከላከያ ሠራዊቱን ለመቀላቀል ለወሰኑ ወጣቶች ሽኝት ተደረገላቸው።

የመከላከያ ሠራዊቱን ለመቀላቀል ተመዝግበው ሽኝት የተደረገላቸው ወጣቶችም መንግሥት የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ያደረገውን ጥሪ ተቀብለው መዘጋጀታቸውን  ገልጸዋል።

ወጣት መልካሙ ድሪባ “አባቶች በጀግንነት ሉዓላዊነቷን ጠብቀው ለዛሬ ያደረሷትንና ያስረከቡንን ሀገር ሰላም ለማስከበር መንግስት ያደረገውን ጥሪ በመቀበል በፈቃዴ ተነስቻለሁ” ብሏል።

“የሀገርን ጥሪ ተቀብሎ ሀገር በፈለገችው መስክ ለማገልገል መቆም እድለኛነት ነው” ብሏል ወጣቱ ።

ሱልጣን መሐመድ በበኩሉ “አባቶች በአሸናፊነት ያቆዩልንን ሉዓላዊት ሀገራችን በኛ ዘመን ለጠላት አትንበረከክም፤ እኛም የኛን ድርሻ ለመወጣትና ሀገራችንን ከመፍረስ ለመታደግ ተነስተናል” ብሏል።

ትላንት በተዘጋጀው የሽኝት ስነ ስርዓቱ ላይ ለወጣቶቹ መልዕክት ያስተላለፉት የዞኑ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ አቶ መኮንን ባይሳ “አባቶች በደምና በአጥንታቸው የገነቧትንናያስረከቧትን ሀገር ዛሬ ደግሞ ሉዓላዊነቷ ሳይነካ በናንተ ውድ ልጆቿ ተከበራ ትቀጥላለች” ብለዋል።

“እናት ሀገራችሁ ዛሬ በእናንተ ስለምትኮራባችሁ እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉ ለወጣቶቹ አድናቆት መቸራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በሽኝት ስነ ስርአቱ ላይ የኃይማኖት አባቶችና አባ ገዳዎች ተገኝተው ወጣቶቹን መርቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.