Fana: At a Speed of Life!

የህወሓት የጥፋት ቡድንን የሚያወግዝና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የህወሓት ቡድን ሀገር የማፈራረስ ሴራን የሚያወግዝ እና የሀገር መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ ሰልፍ በጋምቤላ እየተካሄደ ነው፡፡
በሰልፉ ነዋሪዎቹ “የአብሮነት ጉዟችን በሽብርተኞች አይደናቀፍም”፣ “እኛ ጋምቤላዎች ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን ነን”፣ “ሰላማችን በአንድነታችን ይጠበቃል”፣ “ክብርና ሞገስ ውድ ህይወታቸውን ለሰጡ የመከላከያ ሠራዊት አባላት”፣ “ኢትዮጵያ በጀግኖቿ አፍራ አታውቅም” የሚሉ መፈክሮችን እያሰሙ ነው፡፡
በተጨማሪም “አገር በጁንታው ሴራ አትፈርስም”፤ “የህልውናችን መሠረት የሆነው የህዳሴ ግድባችንን እስከመጨረሻው በመደገፍ ከዳር እናደርሳለን”፣ “ጁንታው የኢትዮጵያ ነቀርሳ ነው” የሚሉ እና በርካታ መፈክሮች በጋራ በማሰማት ላይ ናቸው ።
ሠራዊቱን በሚደግፈውና ሽብርተኛውን የህወሓት ጁንታ በሚያወግዘው ሰልፍ ላይ በርካታ የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች፣ የመንግስት ሰራተኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እየተሳተፉ መሆኑን ከጋምቤላ ክልል ፕረስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.