Fana: At a Speed of Life!

መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና የሽብር ቡድኑን ህወሓት የሚያወግዝ ሰልፍ በደብረ ማርቆስ ከተማ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የምሥራቅ ጎጃም ዞን ነዋሪዎች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እና የአማራ ልዩ ኃይል የሚደግፍ እንዲሁም የሽብር ቡድኑን ህወሓት የሚያወግዝና ሰልፍ በደብረ ማርቆስ ከተማ አካሂደዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌውን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተግኝተዋል፡፡
በሰልፉ ጁንታውን ለመደምሰስ የሚደረገውን ትግል የሚደግፉ፣ የአማራ ክልል መንግስት የክተት አዋጅን ጥሪ የሚያበረታቱ እና የውጭ ጣልቃ ገብንትን የሚያወግዙ መፈክሮች ተደምጠዋል፡፡
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አያሌው÷ ህወሓት የሽብር ቡድን ሀገርን ለማፍረስ እያደረገ ያለውን ሙከራ ለመቀልበስ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ መናገራቸውን ከደብረማርቆስ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.