Fana: At a Speed of Life!

የልደታ ክፍለ ከተማ ባለፉት 15 ቀናት ለመከላከያ ሰራዊት 12 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማ አስተዳደሩ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ለ2ኛ ዙር እየተሳባሰበ ባለው ድጋፍ የልደታ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በአይነትና በገንዘብ ያሰባሰበውን 2ኛውን የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ አስረክቧል::

የክፍለ ከተማውና የወረዳው አጠቃላይ አመራር መዋጮ በማድረግ በተሳተፈበት የድጋፍ ማሰባሰብ ሂደት አስተዳደሩ ዛሬ 200 የሚጠጉ በጎችን ጨምሮ ሌሎች ለምግብነት የሚውሉ ግምታቸው ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ ግበዓቶችን አስረክቧል::

የክፍለ ከተማው ነዋሪዎች፣ ባለ ሃብቶችና አመራሮች ካላቸው ላይ ቀንሰው በራስ ተነሳሽነት ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ሽታዬ ሙሃመድ ተናግረዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ድጋፉን ላሰባሰቡና ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ማቅረባቸውን  ከልደታ ክፍለ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የክፍለ ከተማው ነዋሪ መከላከያ ሰራዊትን በማንኛውም መንገድ ለመደገፍ ያለው ተነሳሽነት የሚበረታታ መሆኑን ጠቅሰው÷ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በተለመደው መልኩ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል::

አስተዳደሩ ለሀገር መከላከያ ሰውራዊት ድጋፍ የሚሆን በገንዘብና በአይነት ከ50 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ ሲሆን÷ ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ከ2 ነጥብ 5ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ቁሳቁስና 10 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ አሰባስቧል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.