Fana: At a Speed of Life!

የሴቶች የፓርላማ ውክልና 50 በመቶ እስኪደርስ ጠንክረን እንሰራለን- ወ/ሮ ሽታዬ

አዲስ አበባ ፣ሃምሌ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሴቶች በፓርላማ ያላቸው መቀመጫ 50 በመቶ እስኪደርስ ጠንክረን እንሰራለን ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ሽታዬ ምናለ ገለጹ፡፡
ወይዘሮ ሽታዬ በአርባ ምንጭ ከተማ የፓርላማ ተመራጭ ሴቶች ኮከስ አባላት ባዘጋጁት የሽኝት መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ ኮከሱ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ጥረት ማድረጉ እንደተጠበቀ ሆኖ አደረጃጀቱ ለሀገር እድገትና ልማት ጠቃሚ በመሆኑ ቀጣዩ ፓርላማ የበለጠ አጠናክሮ ሊያስቀጥለው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ምክትል አፈ-ጉባኤ የተከበሩ ወይዘሮ ሽታየ ምናለን ጨምሮ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ የመንግስት ረዳት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታዎች እና የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ተገኝተዋል፡፡
የኮከሱ ሰብሳቢ ወይዘሮ አበባዬ ገዛኸኝ መድረኩ የተሳካ እንዲሆን የተለያየ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን ማቅረባቸውን ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.