Fana: At a Speed of Life!

ለህዳሴ ግድቡ በ48 ሰዓታት ከዳያስፖራው 70 ሺህ ዶላር ተሰበሰበ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድጋፍ የሚደረግበት ድረ ገፅ ይፋ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ከ583 ዳያስፓራዎች 70 ሺህ 380 ዶላር መሰብሰቡ ተገለፀ፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን፣ ትውልደ ኢትዮጰያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች www.mygerd.com የሚል ድረ ገጽ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ  በ48 ሰዓታት ውስጥ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ 70 ሺህ 380 ዶላር ድጋፍ መደረጉን  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታውቋል፡፡

በተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት÷ድረ ገፁ በተከፈተ 48 ሰዓታት ውስጥ 583 ለጋሾች ለህዳሴ ግድቡ 70 ሺህ 380 ዶላር ድጋፍ አድርገዋል፡፡

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ ÷ድረ ገጹ የፈለጉትን መጠን ማስገባት እንዲችሉ ክፍት የሆነ ሲሆን  36 ሰዎች ግድቡን በተለያየ መንገድ እንደግፍ የሚል  ዘመቻ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡

የተሰበሰበው በአማካኝ በሰአት  ሲታይ 1 ሺህ 510 ዶላር   መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይህ ደግሞ ዲያስፖራው በቁጭት እየደገፈ መሆኑን ያሳያል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.