የሀገር ውስጥ ዜና

በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

By Tibebu Kebede

January 28, 2020

አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጋምቤላ ከተማ በህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር የተጠረጠሩ ሁለት ግለሰቦች ከ17 የጦር መሳሪዎች ጋር  በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ አስታወቀ።

ግለሰቦቹ በቁጥጥር  ስር ሊውሉ  የቻሉት በአንድ መኖሪያ ቤት የጦር መሳሪያዎችን ደብቀው በመገኘታቸው መሆኑን በፌዴራል ፖሊስ የምራዕብ ዳይሬክቶሬት አንደኛ ዲቪዥን ሶስተኛ ሻለቃ ምክትል አዛዥ ኢንስፔክተር ተረፈ በለጠ  ገልጸዋል፡፡

ከተያዙት የጦር መሳያዎች መካከል 11 ታጣፊ ሲሆኑ ÷ ቀሪዎቹ ደግሞ ባለሰደፍ ክላሽንኮቭ ጠብመንጃዎች መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

በአሁኑ ወቅት በግለሰቦቹ ላይ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገባቸው ሲሆን ÷ የምርመራ ሂደቱ እንደተጠናቀቀ ጉዳያቸው ወደ ፍርድ ቤት እንደሚላክ ኢንስፔክተር ተረፈ  ተናግረዋል፡፡

በክልሉ እየተስፋፋ የመጣው ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ለመግታት ከክልሉ የጸጥታ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

ትናንት የታዙትን ጨምሮ ባለፈው ስድስት ወራት 28 የተለያዩ ህገ ወጥ የጦር መሳሪዎችና ከ600 በላይ ጥይቶች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሃላፊው ገልፀዋል።

ምንጭ፡-ኢዜአ