Fana: At a Speed of Life!

መከላካያ ሰራዊትን የሚደግፍና አሸባሪውን ህወሀት የሚያወግዝ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ በሀረር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ነዋሪዎች መከላከያ ሰራዊትን በመደገፍና አሸባሪው ህወሀትን በማውገዝ ታላቅ ህዝባዊ ሰልፍ እያካሄዱ ነው።

ነዋሪዎቹ “ኢትዮጵያ አሸንፋለች፤ ወደፊትም ታሸንፋለች፤ እኛ ሐረሮች ከመከላከያ ሠራዊታችን ጎን ነን፤ ክብርና መጎስ ውድ ህይወታቸውን ለሰጡ የመከላከያ ሠራዊት የሚሉና መሰል መፈክሮችን በማሰማት ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው።

አሸባሪው የህውሃት ጁንታ በዜጎች ላይ እየፈፀመ ያለውን የግፍ ሴራ በፅኑ እንቃወማለን፤ ሀገር በጁንታው ሴራ አትፈርስም የሚሉና መሰል መፈክሮችንም በማስተጋባት የአሸባሪውን የህወሀት ጁንታ ቡድን በዋውገዝ ላይ መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የህልውናችን መሠረት የሆነው የህዳሴ ግድባችንን እስከመጨረሻው በመደገፍ ከዳር እንደርሳለን፤ ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት በድል መጠናቀቅ የበለጠ አነቃቅቶናል ሲሉም ለህዳሴው ግድብ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ባሰሙት ድምጽ አረጋግጠዋል።

ሰልፈኞቹ አሁን ላይ ከከተማው ዋና ዋና መንገዶችና አደባባይዎች ሰልፍ በመለስ በኢማም አህመድ ስታድየም በመሰብሰብ ድምጻቸውን ማሰማት ቀጥለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.