ስፓርት

የአትሌት ለተሰንበት ግደይ የ10ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ፀደቀ

By Melaku Gedif

July 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአትሌት ለተሰንበት ግደይ የ10ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ፀደቀ፡፡

ከአንድ ወር በፊት በሁለት ቀናት ልዩነት ውስጥ ከ15 ሰከንዶች በላይ በሄንግሎ ማጣሪያ ተሻሽሎ በኢትዮጵያዊቷ ለተሰንበት ግደይ እጅ የገባው የ10 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ጸደቀ።

የዓለም አትሌቲክስ የበላይ አካል ታላቁ የኦሊምፒክ ውድድር በቶኪዮ ከተጀመረ ከቀናት በኋላ እንዳሳወቀው÷ ከ4 ዓመት በፊት በሪዮ ኦሊምፒክ ላይ በኢትዮጵያዊቷ አልማዝ አያና ተይዞ የነበረው የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን በ2 አትሌቶች በተከታታይ መሰበሩን ማጽደቁን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!