Fana: At a Speed of Life!

ሜሮን ሀደሮ በደራሲዎች ዘርፍ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ፀሃፊ በመሆን በኤኮ ኬይን ተሸላሚ ሆነች

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ሜሮን ሀደሮ በደራሲዎች ዘርፍ የመጀመሪያዋ ኢትዮጵያዊ ፀሃፊ በመሆን በስመጥሩ ኤኮ ኬይን በተባለ ድርጅት ተሸላሚ ሆናለች፡፡

ሜሮን ሀደሮ ÷ እንደምሸለም ማሰብ ቀርቶ ከሚሸለሙት ዝርዝር ውስጥ መግባቴ በራሱ ትልቅ ክብር በመሆኑ በጣም አስደንግጦኛል ስትል ገልጻለች፡፡

ሜሮን ለዚህ ስራ በተለየ መልኩ ያነሳሳት በችግር ውስጥ ያሉ ሰዎች፣ የስደተኞችን፣ የልማት ተነሺዎችን እና የተፈናቀሉ ሰዎችን ታሪክ መስማቷ እና ማየቷ እንደሆነ ተናግራለች፡፡

በአጭር ታሪክ የመጽሃፍ ዘርፍ ለአሸናፊነት ያበቃትም ጌቱ በሚባል ኢትዮጵያዊ ወጣት ላይ የሚያጠነጥን ነው፡፡

ዳኞቹ በድርሰቱ እንደተደነቁና ከተለመደው አይነት የአፃፃፍ ዘዴ ወጣ ያለና አዲስ እይታን የተከተለ እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሜሮን 13ሺህ ዶላር በሽልማትነት እንደሚበረከትላትም ነው የታወቀው፡፡

ምንጭ ፡- ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.