የሀገር ውስጥ ዜና

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በእንጦጦ ፓርክ ችግኝ ተከላ አካሄደ

By ዮሐንስ ደርበው

July 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የፕላንና ልማት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማት ጋር በእንጦጦ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ አካሂዷል፡፡

የፕላንና ልማት ኮሚሽን ከማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲና የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት የበላይ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በመሆን በእንጦጦ ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ተካሂዷል፡፡

ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ ችግኝ የመትከልና የመንከባከብ መርሃ ግብር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ልማት እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የፕላን እና ልማት ኮሚሽን የአረንጓዴ አሻራን መርር በመከተል ከዚህ ቀደም ለተከታታይ ጊዜያት በአዲስ አበባ እና በሌሎች ክልሎች በተለያየ ስፍራዎች ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ ሲሰራ መቆየቱ ተመላክቷል፡፡

በቀጣይም ችግኞችን የመትከልና የመንከባከብ ተግባሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል መናገራቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!