Fana: At a Speed of Life!

በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች በተያዘው ዓመት መጨረሻ ሀገሪቱን ለቀው እንደሚወጡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢራቅ የሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች በተያዘው ዓመት መጨረሻ ሀገሪቱን ለቀው እንደሚወጡ ተገልጿል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ÷ አሜሪካ በዚህ ዓመት መጨረሻ ላይ ኢራቅ ላይ የነበራትን ተልዕኮ ታጠናቅቃለች ብለዋል፡፡ የኢራቅን ወታደሮች የማሰልጠን እና የማማከር ስራ መስራት ግን እንደሚቀጥል ነው ያመላከቱት፡፡

ባይደን መግለጫውን የሰጡት የኢራቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ አል ካዲኢሚን በነጩ ቤተ መንግስት ጠርተው ካወያዩ በኋላ ነው፡፡

አሁን ላይ ከ2 ሺ 500 በላይ የአሜሪካ ወታደሮች በኢራቅ የሚገኙ ሲሆን÷ ዋና አላማቸውም በሀገሪቱ የሚንቀሳቀሱትን የአይ ኤ ስ የሽብር ቡድን አባላት ለሚዋጉ የሀገሪቷ ወታደሮች ድጋፍ መስጠት መሆኑ ተመላክቷል፡፡

ባለፈው ዓመት የኢራኑ ከፍተኛ ጀነራል ቃሲም ሱሌይማኒ÷ በአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት፣ በኢራቅ ዋና ከተማ ባግዳድ፣ መገደላቸውን ተከትሎ አሜሪካ ሀገሪቷን ለቃ እንድትወጣ ግፊት ሲደረግ መቆየቱ የሚታወስ ነው፡፡

ምንጭ÷ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.