Fana: At a Speed of Life!

በሸካ ዞን ማሻ ከተማ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሰልፍ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በሸካ ዞን ማሻ ከተማ መከላከያ ሠራዊትን የሚደግፍ እና የሽብር ቡድኑን ህወሓት የሚያወግዝ ሰልፍ ተካሄደ።
 
የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልማው ዘውዴ÷ ሁሉም የዞኑ ነዋሪዎች ሀገሪቱን ከጁንታው ጥቃት ለመከላከል ከመንግስት ጎን መቆም እንዳለባቸው አሳስበዋል።
 
የሸካ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አበበ ማሞ በበኩላቸው÷ መከላከያ ሰራዊት ሀገሪቱን ለመጠበቅ እያደረገ ያለው እልህ አስጨራሽ ትግል የሚደደነቅ መሆኑን አውስተዋል።
 
ጁንታው በአንድ ቦታ ብቻ ያለ ሳይሆን በተለያዩ ቦታዎችና ሁኔታዎች የሚታይ በመሆኑ በንቃት አካባቢን እና ሀገርን መጠበቅ እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
እስከአሁን ድረስ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እየተደረገ ባለው የገንዘብ ማሰባሰብ ስራ ከ450 ሺህ በላይ የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀዋል።
 
ሰልፈኞቹ ፈተናዎችን እየመከትን የተስፋ ብርሃናችንን ለማድመቅ እንሠራለን፣ የአሸባሪውን የህወሃት ትንኮሳ እናከሽፋለን፣ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ደማቅ አሻራችን፣ ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘለዓለም ትኖራለች፣ የአብሮነት ጉዟችን በሽብርተኞች አይደናቀፍም፣ በሎአላዊነታቸን ተደራድረን አናውቅም እና የትግራይ ህዝብ አካላችን ጁንታው ጠላታችን የሚሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።
 
በሌላ በኩል ከድጋፍ ሰልፉ በተጨማሪ ወጣቶችና በክብር የተመለሱ የቀድሞ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት እስከ ግንባር ድረስ በመሄድ የሀገር መከላከያን ለመቀላቀል ዝግጁነታቸውን መግለፃቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.