Fana: At a Speed of Life!

በምዕራብ ጎንደር ዞን ለህልውና ዘመቻው ከ60 ሚሊየን ብር በላይ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለህልውና ዘመቻው ከ60 ሚሊየን ብር በላይ መሰብሰቡን የምዕራብ ጎንደር ዞን የሎጅስቲክ ሰብሳቢና አስተባባሪ ኮሚቴ አስታውቋል።

ሀገርን ለማፍረስ የተነሳው የአሸባሪውን የትህነግ ቡድን ለመደምሰስ በምዕራብ ጎንደር ዞን ሕዝቡ በተደራጀ መንገድ በገንዘብ እና በዓይነት ድጋፍ አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል።

በምዕራብ ጎንደር ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ሃላፊና በህልውና ዘመቻው የሎጅስቲክ ሰብሳቢና አስተባባሪ አቶ ደረሰ አዱኛ፥ እንደሀገር የገጠመውን ፈተና ለመወጣት የዞኑ ማኅበረሰብ ከሠራዊቱ ጎን በመቆም ሁለንተናዊ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

እንደ ዞን 143 ሚሊየን ብር በላይ ለመሰብሰብ ታቅዶ አሁን ላይ 60 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብሰቧል ነው ያሉት።

ከዚህ ውስጥ 56 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆነው በጥሬ ገንዘብ የተሰበሰበ ሲሆን፥ 4 ነጥብ 5 ሚሊየኑ ደግሞ በዓይነት የተሰበሰበ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል።

የገንዘብ እና የአይነት ድጋፉ ከነጋዴዎች፣ ከአርሶአደሮች፣ ከመንግሥት ሠራተኛውና ከማኅበራት መሰብሰቡን ነው አስተባባሪው የተናገሩት።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.