Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልልን የደን ሽፋን ለማሳደግ የሚረዳ ንቅናቄ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 21፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልልን የደን ሽፋን ለማሳደግ የሚረዳ ንቅናቄ ይፋ ተደርጓል፡፡
 
የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ከወረዳ እስከ ክልል ያሉ አመራሮች ጋር የ2013 በጀት አመት የስራ አፈጻጸምን ገምግሟል።
 
በግምገማው በበጀት ዓመቱ የተገኙ ውጤቶችና ተግዳሮቶች ላይ ጥልቅ ምክክር ተካሂዷል።
 
በመድረኩ በ2014 ዓ.ም አመራሩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመፍታት የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በሚያስችሉ ጉዳይች ላይም ውይይትና መግባባት ላይ ተደርሷል።
 
የክልል፣ የዞንና ወረዳ አመራሮች ቅንጅታዊ አሰራርን በመከተል ለክልሉ ልማትና ዕድገት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ላይ ተደርሷል።
 
በውይይት መድረኩ የኦሮሚያ ክልል የደን ሽፋንን ለማሳደግ የሚረዳ ንቅናቄ ይፋ ሆኗል።
 
ንቅናቄው የክልሉ የደን ሃብት ላይ የሚደርሱ ውድመቶች ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚረዳ ነው ተብሏል።
 
ከዚህ ባሻገር የክልሉን የደን ሽፋን በማሳደግ ከካርበን ንግድ ገቢ ለማግኘት የሚረዳ መሆኑም ተገልጿል።
 
ለዚህ የሚያግዝ በባለሙያዎች የተደረገ ጥናትም ይፋ ተደርጓል።
 
በክልሉ የደን ሽፋንን ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ አሁን ላይ የኦሮሚያ ክልል የደን ሽፋን 26 ነጥብ 6 በመቶ መድረሱም ተገልጿል።
 
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የደን ሽፋኑ እንዲያድግ የተሻለ አስተዋፅኦ ያበረከቱ አካላትን ማመስገናቸውን ኤ ኤም ኤን ዘግቧል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.