የሀገር ውስጥ ዜና

የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ፀሃፊ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀመሩ

By Meseret Awoke

July 29, 2021

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ጸሃፊና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ማርቲን ግሪፍትስ በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን የስድስት ቀናት ጉብኝት ጀምረዋል፡፡

በጉብኝቱ ወቅት ግሪፍትስ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትን እና ከሰብአዊ እና ለጋሽ ማህበረሰብ ተወካዮች ጋር ተገናኝተው ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በቅርቡ የተሾሙት አስተባባሪው፥ በስራቸው የመጀመሪያውን ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ በማድረጋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡

ማርቲን ግሪፍትስ በቆይታቸው በትግራይ እና አማራ ክልሎች ጉብኝት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ከተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅሀፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!