Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች ሠላማዊ ሠልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ሃምሌ 22፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በአዲስ አበባ የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞች በትግራይ ክልል ኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና እንግልት በመቃወም ሠላማዊ ሠልፍ አካሄዱ።

ኤርትራዊያኑ ስደተኞች በአዲስ አበባ በሚገኘው የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት መስሪያ ቤት ተገኝተው ነው ድምፃቸውን ያሰሙት።

‘በኤርትራዊያን ስደተኞች ላይ የሚደረግ ጥቃት ይቁም፣ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድምፃችንን ይስማ’ እና ሌሎችንም መፈክሮች በመያዝ የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል።

ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በትግራይ ክልል የሚገኙ ኤርትራዊያን ስደተኞችን ከሚደርስባቸው ግፍና በደል እንዲታደጋቸውም ጥሪ አቅርበዋል።

ስደተኞቹ ከዚህ ቀደም በተለያየ ጊዜ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብና ለመንግስታቱ የስደተኞች ድርጅት በደብዳቤና በአካል በመገኘት መልዕክት ብናስተላለፍም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል።

በትግራይ ክልል በሚገኙ ስደተኞች ላይ ግፍና እንግልቱ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ፣ ስደተኞች እየተገደሉና በየጫካው በሽሽት ላይ ያሉትም ለከፋ ችግር እየተጋለጡ በመሆኑ አፋጣኝ መፍትሄ ይሰጠን ሲሉም ጠይቀዋል።

በሠላማዊ ሠልፉ ላይ አካል ጉዳተኞች፣ ሕፃናትና አዛውንት መሳተፋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.