የሀገር ውስጥ ዜና

“ደሜን ለኢትዮጵያየ” በሚል መሪ ቃል ወጣቶች ደም ለገሱ

By Tibebu Kebede

July 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “ደሜን ለኢትዮጵያየ” በሚል መሪ ቃል በተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ ወጣቶች ደም ለግሰዋል፡፡

በብልፅግና ወጣቶች ሊግ ፅህፈት ቤት አስተባባሪነት እየተካሄደ ያለው የደም ልገሳ በተለያዩ የሃገሪቱ አካባቢዎች ተጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን፥ በዛሬው ዕለትም በሲዳማ ክልል ሃዋሳ ከተማ ላይ ወጣቱ በሰልፍ ደሙን በመለገስ ለመከላከያ ሰራዊት አጋርነቱን እያሳየ ይገኛል፡፡

በሌላ በኩል በደቡብ ክልል በከምባታ ጠምባሮ ዞን የሺንሽቾ ከተማ አስተዳደር በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች፣ የከተማዋ የመንግሥት ሠራተኞች፣ የከተማዋ አመራር እና መላው ነዋሪ ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ደም መለገሳቸው ተገልጿል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም ክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች የተወጣጡ ወጣቶች “ደሜን ለኢትዮጵያዬ” በሚል መሪ ቃል የደም ልገሳ ፕሮግራም ማካሄዳቸው ነው የተገለጸው፡፡

የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከብልፅግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!