Fana: At a Speed of Life!

የጉራጌ ዞን ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያዘጋጀውን ድጋፍ አስረከበ

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጉራጌ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት የተበረከተውን ድጋፍ የደቡብ ክልል ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ በዛሬው እለት ተረክቧል።

ድጋፉን ይዘው በሀዋሳ ለክልሉ ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ያስረከቡት የዞኑ ተዋካዮች እንዳሉት እስከ አሁን ከዞኑ ሁሉም አካባቢ 4 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ደረቅ ምግብ፣ ስኳርና ዱቄት የተሰበሰበ ሲሆን ይህን የህብረተሰብ ድጋፍ በዛሬው እለት አስረክበዋል።

የዞኑ ህዝብ በሰላማዊ ሰልፍ፣ በደም ልገሳ፣ በገንዘብና ቁሳቁስ ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ እያደረገ ነው ያሉት ተወካዮቹ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

በዞኑ የወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች በተለይም ደግሞ የከተማዋ ሴቶች 2 ሚሊየን ብር ግምት ያላቸው ደረቅ ምግቦችን በማዘጋጀት ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ያላቸውን አጋርነት በተግባር አሳይተዋል ።

ድጋፉ የተቃጣብን የሉዓላዊነት ጥቃት እስከሚቀቀለበስ ድረስ ተጠናክሮ ይቀጥላል ማለታቸውን የደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

በደቡብ ክልል የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሀብት አሰባሳቢ ኮሚቴ አባላት ድጋፉን በተረከቡበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ እስከ አሁን ከፍተኛ ግምት ያለው ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ይህ ድጋፍ ወደ ማዕከል እየተላከ ይገኛል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.