የሀገር ውስጥ ዜና

በሀረሪ መከላከያ ሰራዊቱን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች ሽኝት ተደረገ

By Tibebu Kebede

July 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽኝት መርሃግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ ፣ የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብዱጀባር መሀመድ፣ የምስራቅ ዕዝ ተወካዮች ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች የሀይማኖት አባቶችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

የሀረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ወጣቶቹ ሀገራዊ ጥሪን ተቀብለው ሀገርን ለማገልገል ላሳዩት ተነሳሽነት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ወጣቶቹ ካለማንም ጫና በፍላጎታቸው መከላከያ ሰራዊትን መቀላቀላቸውም በቀጣይ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ላይ ውጤታማ እንዲሆኑ ከማድረግ አንፃርም የጎላ ሚና አለው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ወጣቶች በስነ ምግባርና በክህሎት ራሳቸውን ማዘጋጀት ይገባል ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በተለይም በሚያደርጓቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን እሴት በማክበር አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የክልሉ መንግስትም ለወጣቶቹ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ መናገራቸውን የሃረሪ ኮሙዩኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል ሽኝት የተደረገላቸው ወጣቶች እንዳሉት መንግስት የሀገር ሉዓላዊነት ለማስከበር ያደረገው ጥሪ በመቀበል በፍላጎታቸው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመከላከል ወስነዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!